ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

በደቡበ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለፋርጣ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 2 ለፋርጣ ወረዳ መንገድ ጽ/ቤት በአዲስና በነባር መንገድ ጥገና ለማሰራት ከወርቄን ቋልሃ-ሶራስ ቀበሌ ከጤና ጣቢያዉ ወደ ማሪያም ቤተክርስቲያን እና ከደብረታቦር ግርቢ የማሽን ጨረታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ግልጽ ጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታስክ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ ሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ይህ ግልጽ ጨረታ ከሚቆይበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ በፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽቤት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት ከዋናዉ ጋር ሊገናዘብ የሚችል ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር) ለማሽን ጨረታ 120,000 (አንድ መቶ ሀያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቸች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመስሪያ ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታ አሽገዉ ፋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ዋ/ ጽ/ቤት ብለዉ በዚሁ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ ከረፋዱ 3፡30 በተዘጋጀዉ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት ሲቻል የሚታሽገዉም በዚሁ ሰዓት ነዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን በ3፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ) በተገኙበት (ባይገኙም) በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊዉ በጥቅል ወይም በተናጥል ሊሆን ይችላል፡፡
  11. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎቹ የሚቀርቡት ፋርጣ ወረዳ ኮምንኬሽን ፑል ንብረት ክፍል እና ማሽኖች መንገዱ በሚሰራበት
    ቦታ የሚገቡ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here