ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል Susan Those butto ourtatio በጀት የካርድ ክፍል ግንባታ፣ ሌሎች የጥገና ሥራዎች የበርና ቁልፍ፣ የመስኮት የቀለም የውሃ መስመር እና የማዋለጃ ክፍል አልሙኒየም ፓርቲሽን በአጠቃላይ የመብራት ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህን መስፈርት የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች (ተቋራጮች)  እንድትወዳደሩ እየጋበዝን በዚህ መሰረት ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ:-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የግንባታ ብቃት ደረጃ 9 ጀምሮ የሆናችሁ እንዲሁም (ቫት) ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
  2. ተጫራቾች ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለዕለት ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. የተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በሁለት ፖስታ ማህተም እና ፊርማ መኖሩን በተጫራቹ ከተረጋገጠ በኋላ ኦርጂናል ኮፒ በማለት በጉልህ ፖስታው ላይ በመፃፍ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከጥር 18/2018 ዓ/ም እስከ የካቲት 02/2018 ዓ/ም 11፡30 በተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው ሳጥን የካቲት 03/2018 ዓ/ም እስክ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዚህ ጨረታ የተወዳደራችሁ በአካል ወይም ተወካይ ባይገኙም ጨረታው በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች ቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት ወይም (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበትን ልዩነት እስከ 25 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  7. ለፋይናንስ ግምገማ ያለፉት ተጫራቾች ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበትን ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ብቻ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚያ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያና 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ወይም በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  9. አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል ዋጋ  ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ሁሉም ለዕድሳት እና ለግንባታው የሚያስፈልጉ የግንባታ እቃዎች በተጫራቾች የሚቀርብ ሁኖ ሥራውን ይሰራሉ፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው የብቃት ደረጃቸው ከ 9 ጀምሮ ካሉት ዝቅተኛ ዋጋ በቀረበው አሸናፈውን እንለያለን፡፡
  12. የሚሰራ የሥራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በማንኛውም ሰዓት በጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋ/ን/አስ/ ቡ/መሪ ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ወይም ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. አሸናፈው ድርጅት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስ/በ/ወ/ዓቃቢ ህግ ቢሮ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ጠቅላላ የተዘረዘሩት ሥራዎች /ግንባታው / በ 60 ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

የጉሃላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here