ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
48

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ግዥ /ፋ/ን/አስ/ደ/የሥ/ሂደት አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቡቶች የጽህፈት መሳሪያ፣ ህትመት፣ የጽዳት እቃዎች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ መኪና መለዋወጫ፣ እና የኮምፒውተር እና ኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ፈርኒቸር የውጭ ስሪት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ለመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፡፡ በእያንዳንዱ ሎት የሞሉትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ያላነሰ ከ2 በመቶ ያልበለጠ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  4. ተጫራቾች የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሠነድ በጥንቃቄ በማሸግ የግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱን የተጫራቹን ስም፣ አድራሻ በመፃፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ለግዥው ፈፃሚ መ/ቤቱ ሠነዱን መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሠነዱን ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ በ4፡30 መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
  8. አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ይዞ ያሸነፈበትን እቃ /አገልግሎት ጥራቱን በጠበቀ መልኩ 1ኛ ደረጃ የሆነውን በተቀመጠዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ገቢ ማድረግ አለበት ከስፔስፊኬሽኑ ዉጭ ለሚሰጥ አገልግሎት የማንቀበል መሆኑ ታውቆ ለሚደርስበት ኪሣራ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  9. ውድድሩ የሚካሄደው በሎት /በጥቅል ዋጋ ስለሆነ ሁሉም የእቃ አይነት በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ዝግ ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 21 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here