ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቻግኒ ከተማ አስተዳደር  ከሚያሰራቸው መሰረተ ልማት ግንባታዎች መካከል አንዱ 04 ቀበሌ የቦሌ ደበታ ድልድይ አፕሮች የጠጠር መንገድ ስራ ሲሆን የዚህን ግንባታ ሎት 2  ቀበሌ 04 ከ ሸህ ያሲን ሙሃመድ ቤት እስከ ወ/ሮ ሞሚና ኡመር ቤት ድረስ ዲዛይን እና ጨረታ ዶክመንት ዝግጅት ስራ በደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አማካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አንድ  ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚሰራውን ሥራ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ አምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ከቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት 2 ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ብቻ፣ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ በመሂ 1 ገቢ በማድረግ  የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ  ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡15 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ጨረታው በወጣ በ16 ተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  10. የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርጎ መመለስ አለበት፡፡
  11. የአብክመ ግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 በተጨማሪ የተሻሻሉ እና የተጨመሩ መመሪያዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
  12. ተጫራቾች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. አሸናፊ የምንለየው በሎት በተሞላው ጥቅል ድምር ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 225 17 21 /058 225 16 31 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡

ቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here