ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት የ2018 ዓ/ም በጀት አመት ለመደበኛ  በጀት አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች /አላቂ የቤሮ እቃዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ህትመት፣ ሎት 5 ልዩ ልዩ የቢሮ ዕቃዎች፣ሎት 6 ፈርኒቸር /ቋሚ እቃዎች/ እንዲሁም ሎት 7 የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በየሎቱ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት አያይዘው ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሽጥበት የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት ብር 20 (ሃያ ብር) በመክፈል በምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ጨረታው ጥር 18/2018 ጀምሮ እስከ የካቲት 02/2018 ዓ/ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ማለትም የካቲት 03/2018 ከረፋዱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታዉ በምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በግልጽ ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  3. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨሪታ ማስከበሪያ በሎት ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ አብሮ በማሸግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ (ኮፒ) በማድረግ ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻው ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተራ ቁጥር 1 በተገለፀው ቦታ እስከ ጥር 02/2018 ከረፋዱ 3፡30 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃውን መጓጓዣ (ትራንስፖርት) እንዲሁም ማናቸውም የመንግስት ታክስ ያካተተ ሆኖ ማቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ካልተገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ከምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በተጨማሪም ከታዘዘው (ስፔስፊኬሽን) እቃ ውጭ ቢያቀርቡ በራሳቸው ወጭ እቃውን ወስደው ቀይረው ማምጣት አለባቸው፡፡
  8. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡ ውል በሚወስድ ጊዜ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት፡፡ በተጨማሪ ወሉን የምትወስዱት ምዕ/ደ/ወ/ፍት/ፅ/ቤት ድረስ በመምጣት መሆኑን  እንገልፃለን፡፡
  9. ፍ/ቤቱ አሸናፊውን በሎት ሆነ በተናጠል የመለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በምዕ/ደ/ወ/ፍ/ቤት ግዥና ፋይናስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 334 06 62 ወይም 09 18 20 13 68 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here