ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
113

በአማራ ክልል  ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት በአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የፍኖተ ሰላም ግብርና ምርምር ንዑስ ማዕከል ተቋርጦ የነበረዉን G+2 የቢሮ ህንጻ ግንባታ  ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውን በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታዉን ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር  ይችላሉ፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ኮፒ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታስክ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚሞሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው፡፡
  1. የሚወዳደሩ ተጫራቾች የሥራ ደረጃቸው BC-4/GC-5 እና ከዚያ በላይ  ደረጃ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአማራ ክልል  ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት  ቢሮ ቁጥር 119 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የስራ ፈቃዳቸውን በማሳየት ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በጥንቃቄ  በማሸግ  በአማራ ክልል  ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት  ለዚሁ ጨረታ  በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን  በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ ከረፋዱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  በየካቲት 03/2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡ 16ኛው ቀን  የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የሥራ ዝርዝር መግለጫው መሰረት በሰነዱ በእያንዳንዱ በግልጽ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፣ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በሞሉት በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው፡፡
  7. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ፣ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. .ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታቸውን በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 114 ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ አማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስትቲዩት  ቢሮ ቁጥር 112 ደረስ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 73 50 34 /09 18 01 77 72 ባሕር ዳር በመደወል  መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፍኖተ ሰላም ግብርና ምርምር ንዑስ ማዕከል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here