ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
83

የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል 2018 ዓ/ም በጀት አመት የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም ሎት የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 የህትመት አገልግሎት ግዥ፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና ሎት 5 አልባሳት ግዥ ለመግዛት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸዉ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለ2018 በጀት ዓመት ዉል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ እንዲሳተፋ ይጋበዛል፡፡

  1. የታደሰና በዘርፋ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የአንድ ጊዜ የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ አቅራቢዎች (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (አምሳ ብር) በመክፍል ግዥ ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተጠቀሰዉ ቀን ዉስጥ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ቢያሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ የሚያሲዙ ይሆናል፡፡ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ 500 ብር የውል ማስከበሪያ 15,000 ብር በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአማረኛ ቋንቋ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በየገጽ በማድረግና ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ ግዥ ፋይናስ ደጋፊ የስራ ሂድት ቢሮ በተዘጋጀዉ የመጫረቻ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ የሚዉለዉ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀን በኋላ በ16 ተኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናስ ቢሮ ከፍል 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አይሰተጓጓልም፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here