ለክብረወሰን የበቃችዉ

0
35

በአሜሪካ ደቡብ ምሥራቅ ስተኒግተን ኬንእና ሊሳ ኖጋሲክ በተሰኙ አሳዳሪዎቿ ቤት የምትኖር “ሜኒ” የተሰኘች ውሻ ሦስት ጫማ ከሁለት ኢንች በተለካ ቁመቷ ለክብረወሰን መበቃቷን ዩፒ አይ ድረ ገጽ አስነብቧል::

“ሜኒ” የሁለት ወር  ቡችላ እያለች ነበር በስተኒግተን አሳዳሪዎቿ ኬን እና ሊሳ ኖጋሲክ ቤት የቤተሰቡ አባል ለመሆን የቻለችው:: እድገቷ ፈጥኖ ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ሲሆናትም ቁመቷ እየገዘፈ በመሄዱ ቤተሰቡ  “ሜኒ” ለክብረወሰን ልትበቃ ትችላለች የሚል ግምት እንዳደረባቸው ተናግረዋል- ለገምጋሚዎች::

የ “ሜኒ” አሳዳሪዎች ቁመቷ እየረዘመ፣ አካሏ እየገዘፈ ሦስት ዓመት ተኩል ሲሆናት በትክክል ለክብረወሰን መብቃቷን እርግጠኛ መሆን ችለዋል::

ከዚህ በኋላ ነበር ለዓለም ድንቃ ድንቃ መዝጋቢ ድርጅት ያስታወቁት፤ መዝጋቢ ድርጅቱም የተገለፀው እውነት መሆኑን ባለሙያዎቹን ልኮ አጣርቷል::

በድንቃድንቅ መዝጋቢ ድርጅቱ ባለሙያ ልኬታም “ሜኒ” ሦስት ጫማ ከሁለት ኢንች ቁመት ማስመዝገቧ ተረጋግጧል:: በዚህም ቀደም ብሎ በሴት ውሻ ቁመት ከፍሎሪዳዋ ውሻ “ሊዛ” ከተያዘው ክብረወሰን በአንድ ኢንች አብላጫ አስመዝግባ  ለክብረ ወሰን መብቃቷን በማደማደሚያነት አስነብቧል- ድረ ገጹ::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 18  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here