ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
71

በደቡብ ጎንደር ዞን የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የሀሙሲት ከተማ አስ/ከንቲባ ጽ/ቤት በሀሙሲት ከተማ ቀጠና 01 አውራ ጎዳና ላይ፣ ቀጠና 04 ጎህ ት/ት ቤት ላይ፣ ሀሙሲት ፖሊስ ጣቢያ ላይ እንዲሁም ሀሙሲት መዘጋጃ ቤት ላይ ያሉ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. ማንኛውም የመግዛት አቅም ያላቸው ተጫራቾች መጫረት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ማንነታቸውን የሚገልጽ ዲጂታል መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  3. የእቃዎችን ዝርዝሩ መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከረዳት ገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ናሙናዎቹን ከላይ በተገለጸው አድራሻ ማየት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በቁርጥ ብር 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሽህ ብር) በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000433908997 ወይም በአባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 4502117448491016 በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ያስያዙትንም የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  6. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንና ማስረጃዎችን ዋናዉን በጥንቃቄ በታሽገ በአንድ ፖስታ ለሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተብሎ ተጽፎበት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የሚታሸገውም በዚሁ ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛዉ ቀን 4፡00 በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዉ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዉስጥ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርቦ የውል ማስከበሪያ በቁርጥ ብር 350,000 (ሶስት መቶ አምሳ ሽህ ብር) በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000433908997 ወይም በአባይ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 4502117448491016 በጥሬ ገንዘብ በማሳያዝ ዉል መዉሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ዉል ካልወሰደ በግዥ መመሪያዉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወሰዳል፡፡
  9. የሚሸጡ ብረታ ብረቶች የሚቀርበዉና ርክክብ የሚፈጸመዉ አይነቱና መጠኑ ከተረጋገጠ በኋላ በሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሃሙሲት ከተማ ላይ ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡
  11. የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ ለሁሉም ዕቃዎች በሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ የሚወስን ሲሆን በሰነዱ የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ የአንዱንም እቃ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  12. ከዋጋ ጥናቱ በታች የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ማንኛውም የአስተዳደርም ሆነ የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው በተጫራቹ በኩል ብቻ ይሆናል፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዘርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ ሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 443 04 00 /09 18 53 10 53 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሃሙሲት ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here