የምሥራቅ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ 1.የጽህፈት መሳሪያ፣ 2. የጽዳት እቃዎች፣ 3. የሥልጠና ማቴሪያሎች /የእንጨት፣ የብረት፣ የግብርና፣ የዕደ ጥበብ፣ የኮንስትራክሽን ማሰልጠኛ፣ 4. ህትመቶች፣ 5. ለታራሚዎች የምግብ እህሎች ለምሳሌ አተር ክክ ለሽሮ፣ ጓያ ክክ ለሽሮ፣ ባቄላ ክክ ለሽሮ፣ በርበሬ ወዘተ፣ 6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ 7. አትክልት 8. ፊኖ ዱቄት እና ሌሎችንም በግልጽ ጨረታ ከህጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የምንፈልገውን አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር ይገኛል፡፡ አንዲሁም ህጋዊ ነጋዴዎች ማሟላት የሚገባቸው፡-
- በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ሽያጭ ለሚፈፅሙ አቅራቢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ድረስ በስራ ሰዓት ምሥራቅ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በየዘርፉ ከገንዘብ ያዥ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ በስራ ፈቃዳቸው መሰረት ማቅረብ የሚገባቸውን የዕቃ ዓይነቶች ለይተው በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመምሪያው ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቧቸው የዕቃዎች ገንዘብ መጠን የጨረታ ማሰከበሪያ አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ሲሆን አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማሰከበሪያ በጨረታ ማስከበሪያ ላይ በመጨመር 10 በመቶ የሚያሲዝ ሆኖ የተሸነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያው በመመሪያው መሰረት የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ከብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ለሆነ ግዥ ከሚከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያው መሰረት 3 በመቶ የሽያጭ ታክስ (ቅድመ ግብር ክፍያ) መክፍል ይኖርበታል፡፡
- በሌሎች ታጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ወቅት ዋጋ የሞሉበት ሰነድ ላይ ፊርማና የድርጅታቸውን ማህተም ማሳርፍ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሽናፊዎች ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል ይዘው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ማረሚያ ቤቱ ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበት ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀን ከቀኑ 11፡30 ታሽጐ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መምሪያው ጨረታውን አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 771 16 36 ደውለው ወይም በአካል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የምሥራቅ ጐጃም ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ

