የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ እንዲሁም ሎት 3 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁ እና በጨረታዉ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ደብረ ማርቆስ በሚገኘው ምስ/ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት አብማ መስመር ዶ/ር ይልቃል ዓይን ህክምና ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት የሥራውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ሞልተዉ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ7ኛው ቀን 11፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡ በ8ተኛው ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ምሥራቅ ጐጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 34 05 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ዞን አልማ ልማት ጽ/ቤት

