የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለእብናት ከተማ አስ/መ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የዉሃ እቃዎች ሎት 2 የማሽን ኪራይ ማለትም ዶዘር ፣ግሪደር ፣ሎደር እና ገልባጭ መኪና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የ2018 የበጀት አመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- ለማሽን ተወዳዳሪዎች በስማቸዉ የባለቤትነት ሊብሬ ያላቸዉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በእብናት ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት በጥሬ ገንዘብ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን የገቢ ደረሰኝ ከኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን ዋና በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርጎ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት/ግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በግዥና ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 እስከ 4፡00 ታሽጎ 4፡10 ላይ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዱ የተዘረዘሩት እቃዎችን በሙሉ የመሙላት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ የአንድንም የእቃ ዋጋ ዝርዝር አለሞሙላት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ድምር ይሆናል፡፡
- የሚገዙ እቃዎችና አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ (ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ እቃ መሰረዝ መደለዝ ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፏቸውን እቃዎችና ማሽኖች መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አቅርቦቶች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ጥራቱ ተጠብቆ ካላቀረበ በመመሪያ መሰረት መ/ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን እንደተገለፀለት በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እብናት ከተማ ገ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ በዝርዝሩ የተጠቀሱትን እቃዎች ብዛት 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእብናት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

