ቤተሰብ የምጣኔ ሀብት አክሲዮን ማህበር እሑድ የካቲት 15/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ ዓባይ ዳር ከሚገኘው የአብክመ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ የአባላት መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ያካሂዳል፡፡ ስለሆነም ባለ አክስዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የስብሰባው አጀንዳዎች
- የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
- የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ
- ዓመታዊ እቅድ ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
- የውጭ ኦዲተር መሾም እና ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ተወያይቶ መወሰን
ማሳሰቢያ፡-
- ወደ ስብሰባው ሲመጡ ሕጋዊ መታወቂያ እንዲሁም ሕጋዊ ተወካዮች ሲመጡ የውክልና ወረቀት እና መታወቂያ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
- ውክልና መስጠት ለሚፈልጉ ቀበሌ 14 አረጋዊያን ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 በሚገኘው ጽ/ቤታችን በመቅረብ ባዘጋጀነው ቅጽ ውክልና መስጠት የሚቻልበትን አማራጭ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ቤተሰብ የምጣኔ ሀብት አክሲዮን ማኅበር

