ሰማይ ጠቀስ ህንፃን ያለ አጋዠ

0
19

አሜሪካዊው አሌክስ ሆኖልድ በታይዋን ዋና ከተማ ታይፔይ 101 ፎቅ ያለውን ህንፃ የደህንነት መጠበቂያም ሆነ አጋዠ ቁስ ሳይገለገል በአንድ ሰዓት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ ወጥቶ ማጠናቀቅ መቻሉን የእንግሊዝ ማሰራጫ አገልግሎት (ቢቢሲ) ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በታይዋን ዋና ከተማ ታይፔ የሚገኘው “ታይፔ 101” በሚል ስያሜ የሚታወቀውን፣ በቀርከሃ ቅርፅ 508 ሜትር ከፍታ ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንፃ ከመሰረቱ እስከ አናቱ በቋሚ (ኮንክሪት) መስታዉት ብቻ ተሸፍኖ የተሰራ ነው፡፡

አሌክስ ሆኖልድ ህንፃውን ጥር 24/2026 እ.አ.አ ቅዳሜ እለት ለመውጣት አቅዶ እንደነበርና በእለቱ በእርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ ማካሄድ ባለመቻሉ አንድ ቀን ተላልፎ በጥር 25/2026 እሁድ  እለት በተሳካ ሁኔታ መፈፀሙ ነው  የተገለፀው – በድረ ገጹ፡፡

ቀደም ብሎ “ቴይፔ 101” ን  “ስፓይደር ማን” 508 ሜትር ከፍታውን በአራት ሰዓታት ውስጥ ወጥቶ አናቱ ላይ መድረሱ  ለንባብ በቅቷል፡፡ ህንፃውን ሲወጣም አጋዠ ቁስ ገመድ እና መቆንጠጫ እንደነበረው ተገልፆል- በድረ ገጹ፡፡

አሌክስ ሆኖልድ  ግን ያለ አጋዠ ቁስ በጥር 24/2026 እ.አ.አ ቀይ ሸሚዝ እና ጥቁር ሱሪ ለብሶ በእለቱ በህንፃው ጫፍ ሰማያዊ ዳራ ፊት ቆሞ መታየት ችሏል፡፡

“ቴይፔ101” ህንፃን አሌክስ ሆኖልድ በወጣበት እለት 89ኛው ፎቅ ላይ ከውስጥ ተመልካቾች በመስኮት ተመልክተውት ፊት ለፊት በመስታውቱ ውስጥ አድናቆታቸውን ለመግለፅ ያሳዩት ድርጊት ጥቂት ትኩረቱን ቢሰርቅበትም ያለመውን በስኬት ማጠናቀቁ ነው ለንባብ የበቃው፡፡

በመጨረሻም የታይዋን ምክትል ኘሮዘዳንት ሺያኦ ቢኪም በኤክስ ገፃቸው የእንኳን ደስ አለህ መልዕክታቸውን የገለጹለት መሆኑ በማጠቃለያነት ለንባብ በቅቷል- በድረ ገጹ፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here