በተራራ አናት ቁብ ያለው ሆቴል ቤት  

0
19

በጣሊያን አልኘስ ተራሮች አናት ከባህር ወለል 4554 ሜትር ከፍታ ላይ የተሰራው እስከ 70 ሰዎች ማስተናገድ የሚችለው ሆቴል ወይም ማረፊያ በአውሮፓ በከፍተኛ ቦታላይ ከተሰሩት ቀዳሚ መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ድረገጽ አስነብቧል፡፡

የማርጋሪታ ማረፊያ ወይም ጐጆ በመባል የሚታወቀው ሆቴል በ1893 እ.አ.አ ነው ተመርቆ የተከፈተው ፤መርቀው የከፈቱት የጣሊያን ንግስት የነበሩት ማርጋሪት ሳቮይ ሲሆኑ መጠሪያውን “ማርጋሪታ ሀት”ም የተሰኘው መነሻው በዚሁ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ከአልኘስ ተራሮች “ፑንታ ግኒፌቲ” በተሰኘው ተራራ ጫፍ በጣሊያን እና በስዊዘርላንድ ድንበር አቅራቢያ በጣሊያን ግዛት ነው የተገነባው፡፡ ግንባታው በመጀመሪያ ላይ በከፍታ ቦታ ላይ የህክምና መድሃኒት ለማጥናት የምርምር ማእከል ለማድረግ ታስቦ ነበር -ዘግይቶ ግን የበለጠ በማስፋፋት ለተራራ ወጪዎች ማረፊያ ሆኗል፡፡

በተራራ ጫፍ የተሰራው ማረፊያ በጣሊያን ከተሰሩት ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ በከፍታ ቦታ ላይ ከተሰሩት ቀዳሚ መሆኑ ነው የተብራራው፡፡ ማረፊያው እስከ 70 ሰዎች የማስተናገድ ዓቅም አለው፤  አገልግሎት የሚሰጠው ከሰኔ እስከ መስከረም መጀመሪያ በበጋ ወራት ብቻ ነው፡፡ በክረምት ግን ለደፋር ጀብደኞች 12 አልጋ ያለው አነስተኛ  ክፍልም ተደርቦ መዘጋጀቱ ተገልፆል፡፡

በ2017 እ.አ.አ ከተራራው ማረፊያ በቅርበት የምትገኘው አላኛ ቫሌሲያ የተሰኘች ከተማ ከንቲባ ለሲቪል ጋብቻ ሥነስርዓት አቅራቢ ደርጅት ማስተናገጃነት  በመፈቀዱ ብቸኛው መዳረሻ ልምድ ላለው ተራራ ወጪ እንጂ ለተፈለገው ዓላማ ሳይውል ቀርቷል፡፡

በተራራው አናት ለመድረስ ተራራ የመውጣት ልምድ እና አካላዊ ጥንካሬ ላለው ሁለት ቀናት እንደሚፈጅም ድረ ገጹ በማደማደሚያነት አስነብቧል፡፡::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here