የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
12

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት የተዘጋጀ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን ማለትም፡- 1ኛ. ቆቦ ከተማ ከድሮው ቴሌ ፊት ለፊት፣ 2ኛ. ቆቦ ከተማ ላልይበላ  ሆቴል ፊት ለፊት (ከደስየ መለሰ ቤት ፊት ለፊት)፣ 3ኛ. ቆቦ ሁለ-ገብ አዳራሽ፣ 4ኛ. ቆቦ ከተማ ከአጌሸን ሱቅ ጀርባ እንዲሁም 5ኛ. ቆቦ ከተማ ዲቃላ -ማዶ የሚገኝ 1000 (አንድ ሽህ ) ካ/ሜ ቦታ ለአልሚዎች በሊዝ ጨረታ ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከየካቲት 02/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች በቆቦ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት  ቅጥር ግቢ ውስጥ የጨረታ ሰነድ መግዛት  የምንትችሉ መሆኑን ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡ በተጠቀሱ ቀናቶች ለማንኛውም መረጃና ቦታውን በአካል ማየት የሚፈልጉ ዘወትር በሥራ ሰዓት በከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቀርቦ ማነጋገር ማየት ይችላሉ፡፡ አጠቃላይ የጨረታ ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተገልጻል፡፡

  1. ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች የተቀመጠውን የጨረታ መመሪያ መሰረት መፈፀም ይኖርበታል፡፡ ከመመሪያው ውጭ የቀረቡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    • በአንድ የጨረታ ዙር ለተመሳሳይ የመሬት አገልግሎት ከአንድ ቦታ በላይ የጨረታ ሰነድ መግዛትና መወዳደር አይችሉም፡፡
    • ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማስገቢያ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ላይ የተመለከቱትን በጥንቃቄ እና በግልጽ ሊነበብ በሚችል መልኩ ማስፈር ይኖርበታል፡፡
    • በግልጽ የማይነበቡ ሥርዝ ድልዝ የበዛባቸው ሰነዶች ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ፡፡
    • በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረትበትን የቦታ ዋጋ በፊደል እና በአሃዝ መሞላት አለበት፡፡ በፊደል እና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ተቀባይነት አለው፡፡
    • ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
    • በጨረታው የሚሳተፈው አካል /ድርጅት ወይም ማህበር/ ከሆነ ህጋዊ የድርጅቱ ማህተም በሰነዶቹ ገፅ ማኖር ይኖርበታል፡፡
    • ተጫራቾች የዋጋ እና የሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዶችን በአግባቡ በሞምላት እና በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ ላይ የተጫራች ስም እና የቦታው ልዩ ፕሎትና የፕሎት ቁጥር በግልጽ በመፃፍ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስገባት ይኖባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
    • የሚቀርበው የቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የጨረታ ዋጋ ለንግድ ከ25 በመቶ ማነስ የለበትም፡፡
    • ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ከጨረታ ውጪ የሚያስደርጉ ድርጊቶች፡-
    • የተጭበረበረ ወይም ከሚፈለገው በታች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች፡፡
    • የተጭበረበረ የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ እና የውክልና ማስረጃ ሰነድ ያቀረበ ተጫራች፡፡
    • በአዋጅ መሰረት በከተማው በወጡ ጨረታዎች አሸንፎ ውል ሳይፈፅም ቀርቶ ገደብና ቅጣት የተጣለበት የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቀ ተጫራች ከሆነ፡፡
    • በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ያስገባ ወይም በጨረታ ዋጋ ላይ ከሌሎች ተጫራቾች ጋር የተመሳጠረ ከሆነ፡፡
    • ተጫራቹ ቀደም ሲል በወሰደው መሬት ላይ 50 በመቶ በታች ሳያጠናቅቅ ሁለት ጊዜ የመሬት የመጠቀም መብቱን ያስተላለፈ መሆኑንና ግንባታ ባለማጠናቀቁ መሬት ተነጥቆ የተወሰነበት የቅጣት ዘመን ያልተጠናቀቀ ከሆነ፡፡
    • የጨረታውን ሂደት የሚፃረሩ ወይም የሚያዛቡ ድርጊቶች የተፈፀመ ሲሆን፡፡
  3. የጨረታ ማወዳደሪያ መስፈርት እና ሌሎች ማብራሪያዎች፡-
    • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የሊዝ ጨረታ ዋጋ 80 ከመቶ ሲኖረው ፤ የቅድመ ክፍያ መጠን 12 ከመቶ እና ክፍያ ማጠናቀቅ ጊዜ 8 ከመቶ ይኖረዋል፡፡ የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሦስቱ ነጥቦች ድምር በሚገኘው ውጤት ነው፡፡
    • ሁለት እና ከዚያ በላይ ተጫራቾች በሶስቱም መወዳደርያ መስፈርቶች እኩል ያመጡ ከሆነ ባቀረቡት የህንፃ ከፍታ የሚለዩ ሲሆን በሁሉም መስፈርቶች እኩል ከሆኑ ግን አሸናፊው በእጣ ይለያል፡፡ በሁሉም መስፈርቶች እኩል ውጥተው ሴት ብቸኛ ተወዳዳሪ ካለች ቅድሚያ ይሰጣታል፡፡
    • አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በአስር የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ቅድመ ክፍያ በመክፈል የሊዝ ውል ይፈፀማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን እና በተጨማሪ በማስጠንቀቂያ በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታው ዋጋ እና ሀሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
    • የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቀን ከየካቲት 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ሲሆን የካቲት 18/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 6፡00 የጨረታ ሰነድ የሚሸጥ ሲሆን ከቀኑ 9፡30 እስከ 11፡00 የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ሆኖ የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው በዚያው ዕለት ከቀኑ 11፡30 ሲሆን ጨረታው በማግስቱ የካቲት 19/2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  ከጠዋቱ 3፡00 ቆቦ ከተማ ሁለ ገብ አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
    • ተጫራቾች ቦታዎችን በአካል መመልከት ከፈለጉ ከጨረታ አስፈፃሚ ቡድን ጋር በመሆን የካቲት 06/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 መጎብኘት ይችላሉ፡፡ ከዚህ ውጪ ባለው ጊዜ በፕላን መመልከት ይችላሉ፡፡

የቆቦ ከተማ አስዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here