በአብከመ ጤና ቢሮ የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ብስኩት፣ የታሸገ፣ ውሃ የጽዳት እቃዎች፣ ህትመትና የጽ/መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 1 ማግኙት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በሰም በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከየካቲት 02/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በደብረ ማርቆስ ደም ባንከ የግ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 የካቲት 17/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- የጨረታ መከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የእቃውን ርክክብ በተመለከተ አሸናፊዉ ድርጅት ደብረ ማርቆስ ደም ባንከ አገልገሎት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የግዥው መጠን (ቫት) የሚገባ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎችንና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉትን ብቻ የሚጋብዝ ይሆናል፡፡
- ውድድሩ በድምር ወይም በሎት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በከፊል የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ላይ ዋጋ መሙላት ከጨረታ ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልከ ቁጥር 058 771 10 50 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደብረ ማርቆስ ደም ባንክ አገልግሎት

