ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

የአ.ብ.ክ.መ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ባለስልጣን ለ2018 ዓ.ም  ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ሎት 2. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ ሎት 5. የተሽከርካሪ ጎማ፣ ሎት 6. የብስክሌት ጎማ፣ ሎት 7. የህንፃ መሳሪያዎች፣ ሎት 8.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና፣ ሎት9.የፎቶ ኤግዚቢሽን፣ ሎት 10. ታፔላ፣ ሎት 11. ሎጎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና የሚጠገኑትንም ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ  መወዳደር ትችላላችሁ ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙም ሆነ የሚጠገኑ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአ.ብ.ክ.መ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ከየካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 16/ 2018 ዓ.ም  በጋዜጣ ታትሞ ስለሚቆይ የጨረታ ሰነዱን በሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን፤ ጨረታው የካቲት 17 /2018 ዓ.ም በ3፡00 ታሽጎ የካቲት 17/2018 ዓ.ም በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው ሊሆኑ ይገባል፤ ይህም በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 218 02 61 ወይም 058 321 13 08 በስራ ቀን መጠየቅ ይቻላል፡፡
  11. አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 11 አባይ ማዶ ባ/ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጎን ኢትዮ ቴሌኮም ፊት ለፊት ነው፡፡

የአ.ብ.ክ.መ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ባለስልጣን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here