ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል የ2018 የበጀት አመቱን ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች ሎት 1. የምግብ አቅረቦት፣ ሎት 2. የልብስ እጥበት አገልግሎት ማቅረብ  የሚችሉ  ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  1. የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የሚቀርቡ የምግብ እና የሚታጠቡ የልብስ እጥበት አይነት አገልግሎት  ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ  ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ግዥ እና ፋይናን ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ  አንድ  በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም (ሲፒኦ) ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሪ ገንዘብ  ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  1. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል  እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ  በታሸገ  ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን  በጋዜጣ ታትሞ ከቆየበት ከየካቲት 02/2018 እስከ የካቲት 16/2018 ዓ.ም ቀን ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም የካቲት 17/2018 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል  ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  1. አሸናፊው የሚለየው በሎት ዋጋ  ነው፡፡
  2. አሸናፊው አገልግሎቱን  ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን የምግብ እና የልብስ እጥበት ዝርዝር  እንጅ ሥርዝ ድልዝ ወሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
  3. አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን  ፍትህ  መምርያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል፡፡
  4. መ/ቤቱ ከተጠየቀው  20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
  5. በመ/ቤቱ ለምግብ እና ለእጥበት  ለአሸናፊው  የሚሰጠው  መብራት፣ ውሀ እና ቤት ኪራይን  በነፃ ሲሆን ከግቢ ውስጥ የመብራት እና የውሀ መጥፋት ቢገጥም በራሳቸው  የሚያቀርቡ መሆኑን  እየገለፅን  ይሄን ታሳቢ በማድረግ  ዋጋውን እንድትሞሉ  ያሳውቃል፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ባለው የምግብ ቤት እና የላውንደሪ ቤት  ገብቶ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
  7. አሸናፊው በመስሪያ ቤቱ ባለው የስነ ምግብ ባለሙያ በሚያቀርበው የሰው ሀይል ብዛት ብቻ ምግብ ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. የልብስ እጥበት በሚሰጠው የቆሸሹ ልብሶች ብዛት ይሆናል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን  በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 00 54 /058 331 01 75 ማግኘት ይችላሉ፡፡

የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here