ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
24

በማዕከላዊ ጐንደር ዞን በጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም፡- 1ኛ. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ሪዞ የማራቢያ ማሽን፣ LCD ፕሮጀክተር፣ ላፕቶፕ፣ ዲስክቶፕ ኮምፒዉተሮች፣ ፍሪጅ፣ ጀኔሬተር፣ ቴሌቪዥን እና ሌሎችም)፣ 2ኛ.የፕሪንተር ቀለም፣ 3ኛ. የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ 4ኛ.የተለያዩ ቆርቆሮ እና ብረታ ብረቶች፣ 5ኛ. የብር ካዝና፣ 6ኛ.ያገለገሉ መጻህፍቶች እና ሞጁል እንዲሁም የተለያየ መጠን ያላቸው የመኪና ጎማ፣ ባትሪ፣ የመለዋዎጫ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ (ድርጅት) በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  2. ተጫራቾች የንብረቱን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግዥና /ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደርበትን የዕቃ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም ከ60 (ስልሳ) ቀን ያላነሰ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ በጥሬ ገንዘብ ካስያዙ ከኮሌጁ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን (መጫረቻውን) ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ስዓት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታዉ በዚህ ዕለት ከቀኑ 10፡00 ታሽጎ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡ ንብረቶችን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ቦታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 10፡00 ድረስ ንብረቶች በአሉበት ንብረት ክፍል በመሄድ በአካል ማየት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታውን አሸናፊ የሚሆነው በተናጠል በተሰጣቸው ተራ ቁጥር መሰረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች ፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማ፣ ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 448 02 34 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here