ለመጀመሪያና ለአራተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በአብክመ በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1∙የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫ ግዥ ለአራተኛ ጊዜ፣ሎት2∙የመኪና ጎማና መለዋወጫ ግዥ ለአራተኛ ጊዜ፣ሎት3∙የጥበቃ የደንብ ልብስ ግዥ ለአራተኛ ጊዜ፣ሎት4∙የጽዳት እቃዎች ግዥ ለአራተኛ ጊዜ፣ ሎት 5∙የህትመት የአገልግሎት ግዥ ለአራተኛ ጊዜ ሎት6∙ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ለአራተኛ ጊዜ ፣ሎት7∙የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ የአገልግሎት ግዥ ለአራተኛ ጊዜ እና ሎት8∙ የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓርት ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው የሚጓጓዘውን ማጓጓዝ፣ የሚገዛውን መግዛት፣የሚሰራውን ማስራት እና የሚሸጠውን መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት፡፡እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጡትን 10 ተከታታይ የሰራ ቀናት እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጡትን ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ  የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው 10 ተከታታይ የሰራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00  ድረስ  የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፣አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ይሆናል፡፡አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመርመር (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ ይምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል፡፡ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ከሀ-ሐ ድረስ ከተዘርዘሩት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንዱ ፊደል ሎት ካለው ቀንሶ መሙላት አይቻልም፡፡
  12. የሰብል ማጓጓዝ የመርክብ ኃላፊነቱን የሚውስድ አጓጓዡ ሲሆን የማስጫኛና ማውረጃ ወጭ አሸናፊ የትራንሰፓርት አይክፍልም፡፡ የትራንስፖርት ማጓጓዝ ወጪ እና መንገድ ላይ የሚከፈል ማንኛውንም ክፍያዎች አሸናፊው ይሸፍናል፡፡
  13. የሰብል ማጓጓዝ ትራንስፖርት የኪሎ ሜትር በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀመጥ ሲሆን ከመነሻው እስከ ማራገፊያው ድረስ ያለው ኪሎ ሜትር ሲሞላ በትንሹም ቢሆን ሊቀንስና ሊጨምር እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ቦታውን አውቃችሁ እንድትሞሉ፡፡ የሰብል ማጓጓዝ ትራንሰፓርተ ጨረታ የሚፈልጉትን ማህበር መርጦ መሙላት ይቻላል ፡፡
  14. የሰብል ማከማቻ መጋዝን ኪራይ ለአራት ወር የሚቆይ ሆኖ የመያዝ አቅሙ ሰላሳ ሺህና በላይ የሆነ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፡፡የመጋዝን ኪራይ አሸናፊ የሚለየው በአንድ ኩንታል ዋጋ ሲሆን ዋጋ የሚሞላው የአንድ ኩ/ል ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ ይሞላ ምክንያቱም አሸናፊ የሚለየው ርዝመት*ቁመት*ወርድ-15%/1.8*10=መጋዝን የመያዝ አቅም ስለሚሰጥ የተሞላው የብር መጠን ሲካፈል መጋዝኑ የሚይዘው የኩ/ል መጠን በማድረግ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን የመጋዝኑ የመያዝ አቅሙ ዩኒየኑ በሚያዋቅረው ኮሜቴ ተለክቶ በሚገኘው መሰረት ይሆናል፡፡የምንከራየው የመጋዝን ኪራይ ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ሆኖ አሸናፊውን በቅደም ተከተል የሚይዝ ይሆናል፡፡
  15. አሸናፊው ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊያቀርብ ነው፡፡ለሰራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊው ይሸፍናል፡፡የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛሉ፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34/09 18 08 26 26 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here