ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
23

የአብክመ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ሎት1∙ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት2 የፈርኒቸር ውጤቶች፣ ሎት3 የፅዳት እቃዎች ፣ ሎት4 የመኪና ጎማና መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፡፡
  2. የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፒስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 ( አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድና የእቃ ሳምፕል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 003 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (ቢን ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበዉ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች በማድረግ በአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ በግዥ /ፋይ/ንብ /አስ/ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን

ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቶች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ የቴክኒካል ፖስታው ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት)ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ይታሸግና ከጥዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል ፡፡ የመክፈቻዉ ዕለት የህዝብ ባዕል እና ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ፡፡
  3. አሸፊዉ ድርጅት የሚመረጠዉ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት) ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
  4. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 18 84 በመላክ ወይም በስልክ ጥበበኛ 058 220 63 50/058 320 86 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ መንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here