ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

የአጅባር መሪ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት ባለዉ የዉስጥ በጀት በአጅባር ከተማ ካናልና ካልቨርት ለስራው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ግብአትም ሆነ የሰው ሃይል በራሱ አቅርቦ የግንባታ ስራውን የሚሰሩ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በመጋበዝ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡  ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በስራ ዘርፉ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው የቫት ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ የስራ ግብር ክፍያ የከፈሉና የግብር መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ስራውን ሙሉ በሙሉ የሚሰራበትን ነጠላ ዋጋ በግልጽ መሙላት አለባቸው፡፡ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ይሆናል፡፡
  3. ደረጃ 7 እና በላይ የስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የስራዉን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሲፒኦ በባንክ ወይም በመ/ቤቱ የውስጥ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ስራውን በጥራት በማጠናቀቅ በሚሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ አለበት፡፡
  6. በስራው ላይ በቂ የስራ ልምድ ያለው ስለመሆኑ እና መልካም የስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
  7. የጨረታ መዝጊያዉ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና ራሳቸዉን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
  8. ጨረታዉን ለማዛባት የሚሞክር ማንኛዉም ተጫራች ቢኖር ከጨረታዉ ዉጭ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም የስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዉርስ ሁኖ በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡
  9. በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡
  10. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆኑ የስራ ልምድ ፣የመልካም ስራ አፈፃጸም የሙያ ብቃት መረጋገጫ እና ከአደራጅ መስሪያ ቤቶች የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ፖስታ ላይ ስማቸዉን ፊርማቸዉን እና የድርጅት ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡
  12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 21 ተከታታይ የስራ ቀናት አጅባር መሪ ማዘጋጃ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመገኘት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቹ የሚጫረትበትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ በ 10/06/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  14. ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 10/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ፡ 033 441 05 23/ 09 14 06 56 11 መደወል ይችላሉ፡፡

የአጅባር መሪ ማዘጋጃ አገልግሎት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here