በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ለ2018 በጀት አመት በዞኑ ሥር ለሚገኙት መምሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ሌሎች እቃዎች /የቋሚ አላቂ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም ሎት 4 ፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባው፡-

  1. የግብር ከፋይ የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ መሂ 1 በማስያዝ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ወይም ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም የሚያስይዙት ዋስትና ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቹ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከሰ/ጎ/ዞን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የተሞላበት ሳይኖረው ኦርጂናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከየካቲት 02/2018 እስከ የካቲት 17/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  8. ጨረታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 የካቲት 18/2018 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ  በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን እቃዎች የሚያቀርበው ለሰ/ጎ/ዞን ንብረት ክፍል የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ የሚወስድ ይሆናል፡፡
  11. የጨረታው መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ  ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ለተጨማሪ መረጃ በስራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 1 ዘወትር በስራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 417 25 44 /058 417 01 26 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here