ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
19

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዋድላ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ሎት 1. የመንገድ ስራ ማሽነሪ ኪራይ፣ ሎት 2. የሶሰት ወር ኮይ ኮይ ዶሮዎች አቅርቦት፣ ሎት 3 ጽ/መሳሪያ፣ ሎት 4 የውሃ ዕቃ እንዲሁም ሎት 5 ሲሚንቶ በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ድርጅቶች ሁሉ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች የተዘጋጀውን እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአዲሱ የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
  6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
  7. ይህ ግልጽ ጨረታ በ16ኛ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግን/አስ/ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትንና ዋጋ የሞሉበትን ሙሉ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን በሚገዙበት ወቅት ናሙና መያዝ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማየት ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ 2 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት አሽናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ባሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በመመሪያው መሰረት ማሲያዝና ወረዳው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ውጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  12. ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 /09 80 51 37 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here