ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ኤሌክትሮኒክስ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 02/2018 እስክ የካቲት 16/2016 ዓ.ም የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 31 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ድምር ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋና ገ/ያዥ በደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ቢሮ ቁጥር 35 የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ የካቲት 16/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የካቲት 16/2018 ዓ.ም  4፡30 ቢኖሩም ባይኖሩም ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. መስሪያ ቤቱ የጨረታ ውጤቱን በጠቅላላ ድምር ውጤት ያያል፡፡
  13. አሸናፊ ድርጅት ንብረቱን ደ/ከ/ስ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  14. ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  15. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 35 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 117 00 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደባርቅ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here