ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ ላለዉ ዉሃ ጽ/ቤት ዉሃ ግንባታ አገልግሎት የሚዉል የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና የሙያ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) ብቻ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይንት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የእቃዉ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከገንዘብ ያዥች ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ባንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ የካቲት 17/2018 ዓ.ም 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 የካቲት 17/2018 ዓ.ም 3፡30 ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 270 05 97 /194 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአለፋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here