የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
20

                                                           የጨረታ ዙር፡ የ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ

                                                             የጨረታዉ ዓይነት መደበኛ ጨረታ

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት ለመኖሪያ 19 (አስራ ዘጠኝ) ቦታዎች፣ ለድርጅት /ለሆቴል/ 26 (ሃያ ስድስት) እና ለወፍጮ 3 /ሶስት/ የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን የካቲት 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለመኖሪያ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለድርጅት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለወፍጮ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በእን/ከ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ከ/መ/ል/ባ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 004 ዘወትር በስራ ቀን እስከ 11፡00 መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቀኑ እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  2. ጨረታዉ የሚዘጋዉ ሰነድ ሽያጭ ባለቀበት ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
  3. ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎችን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በኋላ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ከባለሙያ ጋር መጐብኘት ይችላሉ፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከታሸገበት በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የመኖሪያ በቀጠዩ ቀን የድርጅት በእን/ከ/አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  5. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡ 058 227 00 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳድር ከመ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here