ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
17

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለጓ/ሽ/ወ/ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የመኪና ጎማ፣ ሎት 4. የፕላስቲክ ወንበር፣ ሎት 5. የተማሪዎች ንፅህና መጠበቂያ፣ ሎት 6. የቤትና የቢሮ ዕቃ፣ ሎት 7. የህንፃ መሳሪያ ሎት 8. የአችጊ ጤና ጣቢያ ግንባታ፣ ሎት 9. ዛግራ ቀበሌ የአማ ጎመር አነስተኛ መስኖ ግንባታ ጥገና እና ሎት 10. የውሃ መለዋወጫ አወዳድሮ በሎት ጥቅል መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፈቃድና የቲን ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ስለ እቃው የተዘጋጀውን ስፔስፊኬሽን በትክክል በማጥናት በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሞላት አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  3. በዋጋው ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪል ስም፣ ፊርማና የድርጅቱ አርማ ያለው ማህተም መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪ በፖስታው ላይ ያጫራቹን መ/ቤት ስምና የራሳቸው አድራሻ በትክክል ማስቀመጥ አለበት፡፡
  4. በሌላው ዋጋ ተንተርሶ መወዳደር አይፈቀድም፣
  5. የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ፖስታዎች ላይ የንግድ አድራሻውንና ስሙን በመግለጽ በደንብ በታሸገ ፖስታ በማሸግ የሞላዉን ዋጋ ኦርጅናል ፖስታ የጓ/ሽ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ  ፋይናንስ ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ወይም በመሂ 1 በማስያዝ በፖስታዉ ዉስጥ አሽጎ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ከጨረታዉ ይሰረዛል፡፡
  8. በጨረታው ለተሸነፋ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ውል ከወሰደ በኋላ ይመለስለታል፡፡
  9. አሸናፊው አሸናፊነታችውን ከተገለፀ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉ 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ ካሸነፈዉ ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በመሂ 1 በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. በጨረታ ውድድር ወቅት ቅር የተሰኘ ተጫራች አሸናፊው በተገለፀለት 5 የስራ ቀናት ቅሬታውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ያለ በቂ ምክንያት ውሉን ካፈረሰ ያስያዘውን ገንዘብ በመቀጫ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በህግም እንዲጠየቅ ያደርጋል፡፡
  12. የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ውድድር ጥያቄ ወይም የማስተካከያ ተቀባይነት የለውም፡፡ ማስተካከል የሚቻለው ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን አስቀድሞ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ አስቀድሞ ከጨረታው መውጣት የሚችሉ ቢሆኑም ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡
  14. በጨረታ ሰነዱ የተካተቱ ማንኛውም ሰነዶች ገንጥሎ ማስቀረት አይፈቀድም፣ ይህንኑ ችላ በማለት ተገንጥሎ የቀረበ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፣ ለጨረታ መጓተት በር የሚከፍት በመሆነ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስም፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱ ሙሉ ገጽ መሆኑን ማረጋገጥ ከገዥ ይጠበቃል፡፡
  16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳችውን ማግለል አይችሉም፡፡
  17. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱ በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፍ እንደሚያደርግና ያስያዙት ገንዘብ እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  18. ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  19. ጨረታው በ16 ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  20. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  22. የማስረከቢያ ቦታ ጓ/ሽ/ወ/ ንብረት ክፍል ማስረከብ የሚችሉ፡፡
  23. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  24. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 229 00 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here