ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ

0
24

የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን የፈ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት ለሚያሰራው ሎት 1 የዲች ቦይ 603 ሜትር እና ሎት 2. የዲች ቦይ 365 ሜትር ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መመሪያዎችን ያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም፣ ስምና ፊርማ፣ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን ካርድ ወይም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የተቋራጮች የብቃት ሰርተፊኬት እንዲሁም አድራሻቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ለውጥ ማድረግ ወይም እራሣቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡
  4. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለወደፊት ከመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፍ የሚደረግ ሲሆን ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ የባንክ ሲፒኦ (የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 10፡00 ድረስ ሰነዱን ፈ/ከ/አስ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሽህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የውል ማስከበሪያ 25 በመቶ የባንክ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የግንባታውን ስፔስፊኬሽን እና ዲዛይኑን ከሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡
  11. ተጫራጮቾች በዘርፉ ልምድ የላቸውና ከሰሩበት መ/ቤት የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. ተጫራቾች ሶስትኛ ወገን በመሞላው የዋጋ ሙሌት ትንተርሰው መሙላት አይቻሉም፡፡ ሞልቶ ቢገኝም የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  13. ተጫራቾች ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
  14. ተጫራቾች በጨረታ አከፋፈት ቅሬታ ካላቸው ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ ቀናት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  15. አሸናፊው ድርጅት /ተቋራጭ/ የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት በኋላ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
  16. ተጫራቾች (ተቋራጮች) ምንም አይነት የፍ/ቤት እገዳ ወይም የዲሲፒሊን ክስ ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  17. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ወይም ኦርጅናል እና በኮፒ ማስረጃ በማድረግ ሁለት ፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
  18. ተቋራጮች ጠቅላላ ስራ ተቋራጭና የመንገድ ሥራ ተቋራጭ መሆን አለባቸው፡፡
  19. ስለ ጨረታው የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ 09 12 50 91 06 ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይችላሉ፡፡

የፈንድቃ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here