በአፈ/ከሳሾች እነ አባይ ደምሴ እና በአፈ/ተከሳሾች እነ አበቡ ደምሴ መካከል በመዝገብ ቁጥር 22625 በአለዉ የአፈጻጸም ክርክር ጉዳይ ላይ የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት የሆነዉ በሸበል በረንታ ወረዳ በእድዉሃ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ቱቲ በር ከተባለዉ ቦታ አዋሳኙ በምሥራቅ ተሰማ፣ በምዕራብ ስንታየሁ ካሳሁን፣ በሰሜን ክፍት ቦታ እንዲሁም በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 1350 ካ/ሜ ቦታ ላይ ያረፈ የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 6,307,806.95 (ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰባት ሽህ ስምንት መቶ ስድስት ብር ከዘጠና አምስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ ጫረታው ለ30 ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ መነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ቤቱ ካለበት ቦታ መጋቢት 10/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በአካል ቀርቦ መጫረት የሚችል ሲሆን የጨረታ አሸናፊዉ ወዲያዉኑ 1/4ኛዉን ማስያዝ ያለበት እና ከስም ዝዉዉር ጋር የተያያዙ የሚወጡ ወጭዎችን የጨረታ አሸናፊዉ የሚሸፍን መሆኑ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የሸበል በረታ ወረዳ ፍርድ ቤት

