በአፈ/ከሳሽ ዘንገና የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማህበር ኃ/የተወሰነ እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ በጋሻው ቢተው መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 02 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ ወ/ሮ አዳነች ሰውነት፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን አብዬ እንዲሁም በደቡብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኘውን በአቶ ቢተው ይሁን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ 2,130,000 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር) ይሸጣል፡፡ ስለሆነም በጋዜጣ ወጥቶ 30 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ ከየካቲት 09/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 09/2018 ዓ.ም መጋቢት 09/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 እንዲሸጥ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን በሲፒኦ ይዛችሁ እንዲቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

