ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
17

በወልዲያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በወልዲያ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኘው ማመጫ መስኖ ፕሮጀክት የሚውል የኤሌክትሮ መካኒካል አቅርቦትና ገጠማ ስራ  በዘርፉ በተሰማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በስራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ፣ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተሟላ ዶክመንት ማለትም (የቴክኒካል ) ዶክመንት፣ በኤሌክተሮ መካኒክ ስራ የመልካም ስራ አፈጻጸም ሰርተፊኬት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በተረጋገጠ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ዋና (ኦርጅናል) ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ የተከለከለ በመሆኑ ቢቀርብ ተቀባይነትም የለውም፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ወልዲያ ከተማ መብራት ሃይል ከፍ ብሎ በሚገኘው ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ላይ ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 4፡30 በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡ የጨረታ አሸናፊም ሳምፕል በማቅረብ የቀረበውም ሳምፕል በአማካሪ በኩል መጽደቁ ተረጋግጦ የአቅርቦትና የገጠማ ስራው በራስ ወጭ ሳይት ድረስ ማቅረብ መግጠም ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ብቻ ቅሬታውneማቅረብ ይችላል፡፡
  7. ማንኛወም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክሰን ጨምሮ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ መሙላት ይኖርበታል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
  9. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 13 50 49 72 /09 12 91 82 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here