ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
17

በማዕከላዊ ጎንደር አስተዳደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለጭ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት ሱር ኮንስተራክሽን ኃ/የ/የግል ማህበር አይከል ዙፋን አንገረብ መንገድ ስራ ተቋራጭ የሚጠበቅባቸውን የግብር ግዴታ ከየካቲት 2013 ዓ/ም ጀምሮ ስላልከፈለ በጭልጋ ወረዳ ምርት አንባ ቀበሌ እና አንጓባ ቡላድጌ ቀበሌ የሚገኘውን ንብረትነቱ የሱር ኮንስትራክሽን የሆነዉን ጠጠር በግልጽ ጨረታ አውዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛዉም ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉም ሆነ የሌላቸዉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉም ሆነ የሌላቸዉ፡፡
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚሸጠው ጠጠር ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ተያይዟል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ ቢሮ ቁጥር 7 ከረዳት ገ/ያዥ ድረስ በመምጣት መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ድምሩን 2 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ በመክፈል ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በሲፒኦ ከሆነ በባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ሲፒኦዉ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረቱበት ዋጋ በተዘጋጀዉ ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸዉንና አድራሻቸዉን በመፃፍ በጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥ ንብረት አስተዳደር በድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚዉል ሲሆን ፖስታዉን እስከተገለፀዉ ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛዉ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ዉስጥ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታዉ ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  10. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  11. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥራችን 058 333 11 57 ወይም 09 18 43 38 46 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የድርጅትዎን ማህተም በየ ገፁ ማድረግ አይዘንጉ

የጭልጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here