ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
54

ለወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የሞተር ዘይቶችና ቅባቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቺች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ያሸነፉበት የስራ (የእቃ) ዋጋ ድምር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ ከሆነ 2 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት በመመሪያው መሰረት ይሰበስባል፡፡
  6. ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ አንድ በመቶ በጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) በማስያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለዉጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከየካቲት 16/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 6/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ21 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  12. የጨረታ ሳጥኑ መጋቢት 6/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
  14. መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  16. አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መሰረት ገዝቶ ማቅረብ አለበት፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/1008 ዓ/ም ድረሰ ሲታዘዝ ማቅረብ አለበት፡፡
  18. የተጠቀሰውን ግብዓት በጨረታ አሽናፊው ወጭውን ችሎ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  19. ውድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡
  1. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ 033 331 01 72 እና 033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here