ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
61

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የሚገኘው የአድማስ ሁለ/የገበ/የኀ/ሥ/ማኀበራት ዩኒዬን ኃ.የተ የድርጅቱን ሶፍትዌር ዳታ መረጃ ማስቀመጫ  ሰርቨር እና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳዳሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም  በዚህ ግልጽ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በሙሉ፡-

  1. በጨረታው መወዳደር የሚችሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ ከፍሎ የዩንዬኑ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ የጨረታ ዝርዝር ሠነዱን በመግዛት የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ኢንቨሎኘ (ፖስታ) የድርጅቱን ስም እና ማኀተም በማድረግ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ በተዘረዘረው መሠረት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ያሳውቃሉ፡፡
  4. የጨረታ ተሳታፊዎች የመሸጫ ዋጋችሁን በሠንጠረዥ በተገለፀው ዝርዝር ሁኔታ መሠረት መሙላት የምትችሉ መሆን አለበት፡፡
  5. የጨረታ ዋጋው ከመገለጹ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በባንክ በተረገጋጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. በጨረታ ለተሸነፈ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል፡፡
  7. የጨረታ ሠነዱን ማስገባት የሚጀምረው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ወይም የካቲት 16/2018 እስከ የካቲት 25/2018 ዓ.ም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጐ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መከፈቻው የህዝብ በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  8. አሸናፊው እንደታወቀም የአሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ለውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ5 ቀን ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የጨረታ ማስከበሪያው 2 በመቶ ይወረስበታል፡፡
  9. ከጨረታው ጋር በተያየዘ ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ተገዥ የሚሆኑ መሆኑን መረዳት አለባቸው፡፡
  10. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ 058 227 16 81 /09 98 01 27 00 /09 40 16 16 16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአድማስ ሁለ/የገበ/የኀ/ሥ/ማኀበራት ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here