በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በአዉሮፓ ህብረት እና በመንግስት መቀናጆ በተገኘው የበጀት ድጋፍ በድርማ ወንዝ የመገጭ ወንዝ፣ የክብካብ ስራ መሰረት የእስካቫተር ማሽን ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከየካቲት 16/2018 ዓ.ም ጀምሮ ምስራቅ ደምቢያ ወረዳ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የምንከራየው ማሽን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ድምር በቀረበዉ ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 የካቲት 16/2018 እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ሰነዱን አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት መጋቢት 01/2018 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ፣ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 መጋቢት 01/2018 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
- የማሽኑ ዓይነት ባለሰንሰለቱ ኤክስካቫተር እና በአንድ የስራ ወቅት 3 እና ከዚያ በላይ ይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት እንዲሁም ዋጋው የሚሞላው ነዳጅን ጨምሮ የማሽን ማጓጓዣ እና ሌሎችንም በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- የሚሰራዉ የመገጭ ወንዝ 8 ኪ/ሜትር 1068 እና የድርማ ወንዝ 4 ኪ/ሜትር ሆኖ 534 ሰዓት ነዉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች (ተወዳዳሪ) አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ቀርቦ ውል መውሰድ እና ወደስራ መግባት አለበት፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 32 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከተዉም
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

