ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
61

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የቻግኒ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት  ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 ደንብ ልብስ፣ ሎት 5 ህትመት፣ ሎት 6 የዉሃ እቃ፣ ሎት 7 ኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት 8 የመኪና ጎማ እንዲሁም ሎት 9 ፈርኒቸር ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳድር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለቸው፡፡
  2. የግብር ከፈይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200.000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የዕቃዎች (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከተቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቸቻው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ሰነዱን ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የእለት ገቢ ስብሳቢ ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መጫረት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ሰነዱን በመሙላት ከሌሎች ማስረጃዎች ጋር በአንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሽግ ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ለግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 በ16 ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ በዚያው ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሰይ ሰዓት ተሸጎ በተመሳሰይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም አድርጎ መመለስ አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃዎች በተሰጠዉ የግዜ ገደብ ጨርሶ የማሰረከብ ግዴታ አለበቸው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቁ ነው፡፡
  14. ውድድሩ በሎት (ጥቅል) ድምር መሆኑን አውቀው የተጠየቁትን የስራ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ እንዲሞሉልን እንጠይቃለን፡፡
  15. እቃዎች ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ድረስ ንብረት ክፍል በማምጣት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  1. ሰለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 556 20 09 ወይም ቻ/መ/ደ/ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 47 ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጀ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here