ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
62

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት ዓመት የህትመት ሥራዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ብትን ጨርቅ፣ የዉሀ እቃዎች፣ ኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ጥበቃ እና ጽዳት አውት ሶርስ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥዉ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 50 (አምሳ ብር) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ሰነድ በመግዛት ከግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 86 መዉስድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃዎች (አገልግሎት) በተሰጠዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት ያለባቸዉ ሲሆን ናሙና ለሚያስፈልጋቸዉ የተለያዩ እቃዎች ሆስፒታሉ በሚያቀርበዉ ናሙና መሰረት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ዕቃ /አገልግሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሆኖ የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ በመፈረም ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛዉ ቀን እስከ 3፡30 ድረስ በሆስፒታሉ ከግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 86 በሚገኘዉ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡ በ16ኛው ቀን ጨረታዉ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታዉን ይከፍታል፡፡ የጨረታዉ ሰነድ መግዛት የሚቻለዉ እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. መ/ቤቱ ጨረታዉን በሎት የሚያወዳድር ሲሆን በአንድ ምድብ ዉስጥ ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ዉስጥ ሳይሞሉ መተዉ አይቻልም፡፡ በሎት ያልሞላ ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፏቸዉን ዕቃዎች (አገልግሎት) ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 ስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበዉ ዉል መያዝ አለበት፡፡
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. የጨረታዉ ተሳታፊዎች ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 86 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 77 44 51 /09 04 56 00 11 መደወል ይችላሉ፡፡

ደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here