የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግቢው ውስጥ የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለህጋዊ ነጋዴዎች መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደስ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና ጠቅላላ ዋጋው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ መቆያ ጊዜ ከየካቲት 16/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2018 ዓ/ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሲሆን ተጫራቾች ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከየካቲት 16/2018 ዓ/ም እስከ የካቲት 30/2018 ዓ/ም እስከ 11፡30 ብቻ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን መጋቢት 1/2018 ዓ/ም 3፡30 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን 3፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ለመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፋ በተገለጸ ከአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ሌሎች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዩች ካሉ በግዥ መመሪያ የምንገዛ ይሆናል፡፡
- የማስመዘኛና የማስጫኛ ወጭዎች በአሸናፊ ድርጀቶች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ መረዳት ይችላሉ፡፡
የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

