ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
177

በሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር የከተማ ፋርማሲ G+4 ህንፃ ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ደረጃ 4- GC እና BC እና ከዚያ በላይ የሆኑ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡ ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል ከግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 18 ላይ በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን ለየብቻ በአንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፁሁፍ በታሸገ ኢንቨሎና አድራሻን በመጥቀስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የአንድ ዓመት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 5 ከመቶ
  5. ተጫራቾች ከአሰሪ መ/ቤቱ የተሰጠ የመልካም የስራ አፈፃፀም በ2016 ዓ/ም ጀምሮ ቢያንስ ሁለት የስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 3 ከመቶ
  6. የፋይናንስ አቅምን በተመለከተ የድርጅቱን የአሁን የፋይናንስ ብቃትና አስተማማኝ የትርፍ ሁኔታን ለማረጋገጥ እንዲቻል ተጫራቾች የተከታታይ አምስት የበጀት አመታት በተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ የተሰራና በገቢዎች ወይም በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 10 ከመቶ
  7. ተጫራቾች የድርጅቱን አማካኝ የተከታታይ አምስት ዓመት የኮንስትራክሽን ገቢ በክፍያ የምስክር ወረቀት የተረጋገጠ 80 ሚሊዮን ብር ብቻ ማቅረብ አለበት፡፡ 20 ከመቶ
  8. የፋይናንስ አቅምና ምንጭን በተመለከተ ተጫራቾች የፋይናንስ ስራ ካፒታሉን የ100 ሚሊዮን ብር ከፋይናንስ ተቋም የተረጋገጠ የገንዘብ ብድር ማረጋገጫ ወይም የተቀማጭ ገንዘብ ማሳያ (cash statement) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 8 ከመቶ
  9. ተጫራቾች ለስራው የሚያገለግሉ ማሽነሪዎች ማለትም ኤክስካባተር፣ ሎደር፣ ግሪደር፣ ሲኖትራክ፣ ኮንክሬት ሚክስር፣ ባይብሬተር እና ሌሎች ወሳኝ የግንባታ ማሽነሪዎች የተገዙበት ህጋዊ ደረሰኝ ወይም የኪራይ ውል ማቅረብ የሚችሉ፤ 8 ከመቶ
  10. ተጫራቾች ለስራው ዝርዝር የስራ እቅድ ማቅረብ ይኖርባቸውል፡፡ 5 ከመቶ
  11. ተጫራቾች ባለፉት ሶስት አመታት የበጀት መጠናቸው 35 ሚሊዮንና በላይ የሆነ በቀጥታ ተቋራጭነት ወይም በጥምር ተቋራጭነት የሰራ መሆን ያለበት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ቢያንስ ሁለቱ 100 በመቶ የተጠናቀቀ ሌላው 80 በመቶ በላይ የደረሰ መሆኑን የሚገለጽ ማስረጃ ከአሰሪው ተቋም ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 20 ከመቶ
  12. የሰው ኃይልን በተመለከተ ተጫራቾች ስልጣን ባለው መ/ቤት የጸደቀ ዝርዝር የሰው ኃይል የቅጥር ውል ለወሣኝ የግንባታ ዘርፎች ማለትም ፕሮጀክት ስራአስኪያጅ፣ ቢሮ መሃንዲስ፣ ሳይት መሀንዲስ፣ ኤሌክትሪካል መሀንዲስ እና ፎርማን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የሥራ ውሉ ዝርዝር የሥራ ልምድ በተጠቀሰው የሥራ መደብ ላይ የሰሩ መሆኑን በመግለጽ የሥራ ልምድ አብሮ መያያዝ አለበት፡፡ 15 በመቶ
  13. የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ተጫራቾች የግንባታ ሥራውን በሚያከናውኑበት ጊዜ የግንባታ ሥራውን ከሚያከናውኑበት ከባቢ ጋር የተስማማ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህን የሚያረጋግጥ የግንባታ ከባቢ ተስማሚነት ማረጋገጫ እቅድ ማቅረብ አለበት፡፡ 6 ከመቶ
  14. ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  15. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ር ቢሮ ቁጥር 18 በ22ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  16. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያ ዝርዝር ላይ ያልተገለጸ ቢኖር በግዥ መመሪያዉ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 በአካል በመገኘት ወይም በመላክ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡

የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here