በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የሚገኘው የጎህ ሁለ/የገበ/ኅ/ስ/ማህበራት ዬኒየን ኃ.የተወሰነ የእንስሳት ምጥን መኖ ለማምረት አገልግሎት የሚውል ጥሬ ዕቃ 1ኛ. በቆሎ 1,200 ኩ/ል፣ 2ኛ. የኑግ ፋጉሎ 600 ኩ/ል፣ 3ኛ. የአኩሪ አተር ፋጉሎ 600 ኩ/ል፣ 4ኛ. የሱፍ ፋጉሎ 300 ኩ/ል፣ 5ኛ. የስንዴ ፉርሽካ ኪሎ 200 ኩ/ል እና 6ኛ. የምግብ ጨው 30 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጥቅል ዋጋ መሰረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ 2 በመቶ በባንክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋሰትና) አስይዘው ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ከዩኒየኑ በጥሬ ገንዘብ በገቢ ደረሰኝ የሚያሲዙ ከሆነ የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚወዳደሩበት ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከዬኒየኑ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አለባቸው እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ይሰጣል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖራው የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋውን ሞልተው በፖስታ አሽገው ከዬኒየኑ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በወቅቱ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ዋጋ ሆኖ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን እስከ 6፡30 ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡40 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ አስይዞ በ5 ቀን ውስጥ ከዬኒየኑ ቀርቦ ውል መውስድ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪው ያሸነፈበትን ጥሬ ዕቃ ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ደብረታቦር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዝን ድረስ የንብረቱን ደህንነት ጠብቆ ሳይጎድልና ሳይበላሽ በራሱ ትራንስፖርት አጓጓዞ ማቅረብ ወይም ማስረከብ አለበት፡፡ እንዲሁም ጥሬ ዕቃውን ለዩኒየኑ ንብረት ክፍል ሲያስረክብ የማስወረጃ የሰራተኛ የጉልበት ክፍያ ወጭን አሸናፊው ድርጅት /ግለሰብ ይሸፍናል፡፡
- ዪኒየኑ ያወጣውን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 እና 058 141 99 27 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ደ/ታቦር ከተማ ጸደይ ባንክ ዲስትሪክት አንደኛ ፎቅ ነው፡፡
ጎሕ ሁለገብ የገበ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

