ድርጅታችን ጎሕ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃ.የተ 1ኛ. ሩዝ ቀይ እና ነጭ ያልተመሸነ ብዛት 4,832 ኩ/ል፣ 2ኛ. ጤፍ 3,409፣ 3ኛ. ስንዴ ብዛት 167 ኩ/ል፣ 4ኛ. የቢራ ገብስ 423 ኩ/ል፣ 5ኛ. የጥራጥሬ እህል ብዛት 250 ኩ/ል በድምሩ 9,081 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዚህ ንግድ ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (ዋስትና) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆኖ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ መገናኛ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማ ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን እና የተጫራቾች መመሪያውን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከጎህ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተወሰነ ገዝቶ በመውሰድ የመወዳደሪያ ዋጋ፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን ሰነዶች አሟልተው እና ዋጋቸውን ሞልተው በፖስታ በማሸግ ከዩኒዬኑ ቢሮ ደ/ታቦር በጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ፀደይ ባንክ ደ/ታቦር ዲስትሪክት ህንጻ 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱ ተሸጦ በ10ኛው ቀን መጨረሻ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት በ840 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 7ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የምርቱን ናሙና ማየት ለሚፈልግ ደ/ታቦር እና ይፋግ ከሚገኘው ከዩኒየኑ መጋዝን ማየት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ የሞላ (ያቀረበ) ሲሆን አሸናፊው በተለየ በ5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪ የጠቅላላ የዋጋውን 10 በመቶ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡
- ዩኒዬኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ምርቱን የሚረከበው ከዩኒዬኑ መጋዘን ሲሆን የትራንስፖርት እና የወዛደር በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በኀብረት ሥራ ማህበራት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 13 36 /058 141 99 27 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎሕሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተወሰነ

