በሰሜን ወሎ መስተዳደር ዞን መምሪያ የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስተዳደር ቡድን ለወረዳዉ ሴክተር መ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ እና የዳዉንት ወረዳ ስራና ስልጠና ተቋም በመደበኛ በጀት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለሚያስገነባዉ የኤሌክትሪክ ወርክ ሾፕ እና የእንጨት ስራ ወርክ ሾፕ ግንባታ ግንባታ እንዲገነባላቸዉ ባሳወቁን መሰረት ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውን በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አዉጥቶ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግንባታ ማስገንባት እና የጽህፈት መሳሪያ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የዳውንት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን ለግንባታዉ ከደረጃ አምስትና ከዚያ በላይ ያሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ኦርጅናልና ኮፒ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ ሴት ታስክ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚሞሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ብር 450,000 (አራት መቶ ሀምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ህገዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- በማንኛውም ግዥ ከብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በላይ እና ለአገልግሎት ግዥ ከብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) በላይ 3 በመቶ የቅድመ ግብር ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ለተገለፁትን ግንባታዎች የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 15 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 22 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ዳ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ማለትም መጋቢት 07/2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ለቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የስራ ዝርዝር በመግለጫው መሰረት በሰነዱ በእያንዳነዱ በግልጽ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፣ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሞሉት የግንባታ እና የጽህፈት መሳሪያ ሰነድ ላይ በነጠላ ዋጋም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ ያስያዝቱን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንደማይሳተፉ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 15 ደረስ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 033 241 91 37 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅሬታቸውን በየደረጃው ላለ የፋይናንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

