የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት አመት አመታዊ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የአገልግሎት መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 8 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበራያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ከየካቲት 16/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን መጋቢት 01/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ታሽጐ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በግንባር ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 775 10 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ
የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

