ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
159

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት በኮሌጁ ውስጥ የሚገኘውን የስብሰባ አዳራሽ፣ የሰራተኞች መዝናኛ ላውንች፣ ከመማሪያ ብሎኮች የተወሰኑ ክፍሎች እና አስተዳደር ህንፃ በከፊል የዕድሳት እና ጥገና ለማሰራት GC እና  BC ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ  ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን  በግልጽ የጨረታ  አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች በመሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር (ቲን) የተሰጣቸዉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ እና እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ባዘጋጀው የጨረታ መመሪያና ስፔስፊኬሽን መሰረት መጠገን የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡ የሚያድሱበትን እና የሚጠግኑበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ ቅፅ ሞልተው ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የምታሲዙ ከሆነ በገቢ ደረሰኝ ገቢ አድርጋችሁ የደረሰኙን ኮፒ ከሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ  ከየካቲት 16/2018 እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም 11፡00 ድረስ እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስ/ቡድን  ቢሮ ቁጥር 1 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥ ላይ ተሳትፈው በውለታቸው መሰረት ባለመፈፀማቸዉ ምክንያት ስልጣን ባለው አካል እገዳ ያልተደረገባቸው መሆን አለበት፡፡
  7. የጨረታ ሳጥኑን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት መጋቢት 01/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡45 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በመክፈቻዉ ዕለት ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. አሸነፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ግዥ ፈጸሚ አካላት ከአሸናፊው ተጫራች የሚጠገነዉን የጥገና መጠን ወይም ብዛት 20 በመቶ መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  10. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ ይሆናሉ፡፡

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here