የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተለያዩ አገልግሎት የሚሆን ለኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሪክ ሲቲይ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ለማንፋክቸሪንግ፣ ለሆቴል ቱሪዝም እና ለኮሌጁ ለህፃናት ማቆያዉ ክሊኒክ አገልግሎት የሚዉሉ ጥሬ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በተናጠል መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ የሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና የሥራ ዝርዝሩን ዓይነት ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ዉድድሩ በተናጠል ዋጋ ሆኖ አሸናፊ የሚለየው ዝቅተኛ ዋጋ የሚያቀርበው አሽናፊ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉትን ድርጅት እቃዎችን በራሱ ወጭ በማጓጓዝ በሙያተኞች እየተረጋገጠ ዕቃዎችን ገቢ ያደረጋል፡፡
- የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ወይም ገጽ ላይ ፊርማ እና የድርጅቶች ማህተም በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ 2፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ቀን ከየካቲት 16/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2018 ዓ.ም 2፡30-11፡00 እንዲሁም በመጋቢት 01/2018 ዓ.ም እሰከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ክፍል መጋቢት 01/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡05 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ የሚፈልጉ ግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ቁጥር 058 111 83 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

