ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
116

ምሥራቅ ጎጃም አሥተዳደር ዞን የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አሥ ቡድን ለእነማይ ወረዳ መንገድ እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በ2018 በጀት በመደበኛ ካፒታል  ሎት 1 ከብቸና ከተማ ብቸና ደብር ባንጃ ሽረር 15፣ ባንድ ደንሳ 13 ኪሜ የመንገድ ጥገና በደረጃ RC/GC 5 እና በላይ የሆነ ሙሉ ማሽነሪውን እና የሰው ሃይል ራሱን ችሎ የሚሰራ፣ ሎት 2 በእነ ወ/ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ስር ለሚገኘው በካፒታል በጀት ለየትመን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የOPD ግንባታ BC/GC ደረጃ 5 እና በላይ የሆነ፣ ሎት 3 በእነማይ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ስር ለሚገኘው ለየትመን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አንድ ብሎክ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች መማሪያ ክፍል ግንባታ በካፒታል በጀት በደረጃ GC/BC 6 እና በላይ የሆነ፣ ሎት 4 የእነ/ወ/ግብርና ጽ/ቤት በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በእንደሽኝት ቀበሌ እነክርክር ጎጥ አነስተኛ ጥልቅ የእጅ ጉድጓድ ግንባታ በደረጃ WWር-7 እና በላይ የሆነ ግንባታ ለማስገንባት፣ ሎት 5  የኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና እንዲሁም ሎት 6 የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 5 እና 6 በስተቀር ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾችን ማንኛውንም የሚያስወጣ ማቴሪያልም ሆነ የስው ሀይል ተጫራቾች በራሳቸውን ችለው ለማስራት እና ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ለሎት 5 እና 6 የግዥ መጠኑ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተቋራጭ የታደሰ የግንባታ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቹህ፡፡
  4. መ/ቤቱ ከጨረታው አሸናፊው ላይ 3 በመቶ ታክስ የሚቆረጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  5. ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ላሉ ሎቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፤ ምንም አይነት የግንባታ ሥራ ካልሰራ ላለመሰራቱ ከሚመለከተው መ/ቤት ደብዳቤ ያስጻፈ መሆን አለበት፡፡
  6. ከሎት 1 እስከ ሎት 4 አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ከመሃንዲስ ግምት 25 በመቶ በታች ካልሆነ አጠቃላይ ከተወዳደሩበት 10 በመቶ የባንክ በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ሲኖርበት ከተዘጋጀው የመሃንዲስ ግምት ዋጋ አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ከ25 በመቶ ዝቅ ብሎ ካቀረበ ለውል ማስከበሪያ 25 በመቶ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ሎት 1 እስከ ሎት 4 በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ወይም ተቋራጭ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ ost (breakdown) እና የግንባታ መርሃ ግብር (project work schedule) እንዲሁም ባቀረበው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ (conformation letter) አሸናፊነቱ በተገለጸ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  8. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ለእያንዳንዱ ሎት ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ለሎት 4 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለሎት 5 እና 6 ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ፋይናስ ቡድን ገ/ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውን ማስረጃ እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቹሀል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ እንዲታወቅ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) ብቻ ሎት 4 ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) ብቻ ሎት 5 እና 6 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ ገንዘቡን በመቤታችን መሂ 1 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  10. ከሎት 1-4 ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ31ኛው ቀን ከሎት 5-6 ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝም የጨረታውን መከፈት የሚያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን እሁድ ቅዳሜ እና የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ፖስታ ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያውን በመጨመር ቴክኒካል ዶክመንቱን ፋይናንሽያል ዶክመንቱን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቹሀል፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት እነ/ወ/ዐቃቢ ህግ የሚያስከፍለውን የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ወጭ መሸፈን አለበት፡፡ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጅምሮ የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡ እንዲሁም ለእቃዎች የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ40 ቀናት ይሆናል፡፡
  12. ከሎት 1 እስከ ሎት 4 አሸናፊ የሆነው ተጫራች በራሱ ወጭ በእንግሊዘኛ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እና የመሀንዲስ ግምት ከህጋዊ ትርጉም ቤቶች ወደ አማርኛ ማስተርጎም ይኖርባቸዋል፡፡
  13. አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ዋጋ ጥቅል ድምር ዝቅትኛ ዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ተጫራቾች አጠቃላይ የስራ ዝርዝር እና ዲዛይን ከሰነዱ ጋር አብሮ የተያያዘ መሆኑን እንዲታወቅ፡፡ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ እንዲሁም ፓራፍ ቢያደረግም ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ በጨረታ ስነዱ በዋጋ መሙያው እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  14. ለሎት6 በባለሙያ የሚረጋገጡ እቃዎች በባለሙያ እየተረጋገጡ የምንረከብ መሆኑን እና አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈውን እቃ እነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስር ካለው ንብረት ክፍል ድረስ አስፈላጊውን ወጭ በመሸፈን ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 665 01 00 /08 ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here