የታማሚዎችን እንክብካቤ የሚያሻሽለው

0
79

በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት የመንፈስ ጭንቀት ሥር የሰደደ የደም ሥር ሥርዓት ከማድከም ወይም የመርሳት በሽታ ከመጀመሩ በፊት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ስለሚችል ሁነቱን መገንዘብ የህሙማኑን እንክብካቤ ማሻሻል እንደሚያስችል ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ለንባብ አብቅቶታል::

በቻይና የሻንጋይ ጂያኦ ቶንግ ዩኒቨርሲቲ በመረጃ ምንጭነት ለህትመት እንዳበቃው የፓርኪንሰን የነርቭ ስርዓት መድከም እንዲሁም “ዳመንቲያ”መርሳት በሽታ እና ለተዛማጅ የጤና ችግሮች ከመጋለጥ በፊት የሚከሰት የመንፈስ ጭንቀት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይችላል:: ይህንን ተገንዝቦ ለመንፈስ ጭንቀቱ ወይም ለቅድመ ማስጠንቀቂያው መፍትሄ መሻት የታማሚዎችን ህይወት ያሻሽላል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ::

ተመራማሪዎቹ ከ2007 እስከ 2019 እ.አ.አ. ባለው ጊዜ በ “ፓርኪንሰን” እና  በ“ዳመንቲያ” የተያዙ 17,711 ግለሰቦች ላይ ክትትል እና ጥናት አካሂደዋል:: በተገኘው ውጤት የመንፈስ ጭንቀት በሌሎች  በሽታ ከተያዙት በበለጠ የ “ፓርኪንሰን” የነርቭ ስርዓት መድከም እና መንቀጥቀጥ እንዲሁም በ “ዳመንቲያ” የዓእምሮ መናጋት፣ ማገናዘብ አለመቻል ከማጋጠሙ አስቀድሞ በተደጋጋሚ መከሰቱን ተገንዝበዋል::

ግኝቱ ድብርት ወይም የመንፈስ ጭንቀት ከጤና ማሽቆልቆል ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የሥነልቡና ምላሽ ሣይሆን በአንጐል ውስጥ ቀድሞ ከሚታይ የነርቭ ሥርዓት ለውጥ ጋር ሊገናኝ እንሚችል አመላክቷል::

ተመራማሪዎቹ የመንፈስ ጭንቀት ያለበት ሰው ሁሉ የ “ፓርኪንሰን “በሽታ ወይም  “ዳመንቲያ” ያጋጥመዋል ማለት እንዳልሆነ አፅንኦት ሰጥተው በሌላ በኩል ድብርት ወይም የመንፈስ ጭንቀት ለመጀመሪያ ጊዜ በአረጋውያን ላይ ሲከሰት ከሌላው ጊዜ በበለጠ በቅርበት መርዳት  እና ክትትል ማድረግን ግድ እንደሚል ነው ያደማደሙት::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here