ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
97

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የካቲት 09/2018 ዓ.ም በታተመው በኩር ጋዜጣ የወጣውን ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነዱን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የተሻሻለው ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ሎት 1. የተለያዩ የውሃ ቆጣሪዎች፣ ሎት 2. የአፈር ቁፋሮ አገልግሎት ሰራ እንዲሁም ሎት 3. የተለያየ መጠን ያላቸው ሰመር ሰብል ፓምፕ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (የታደሰ) የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል ኦርጅናሉን፣ ኮፒውን እና ሲፒኦ በተለያየ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ብቻ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /un Conditional  Bank Garanty/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የለባቸውም፡፡
  7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡  15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር  05 83 20 50 79  ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here